የወጣቱን ስብዕና ለመቅረጽና ሀገርን ለማሻገር ያለመ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ!

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016


“የለውጥ ትውልድ” የተሰኘ የወጣቱን ስብዕና ለመቅረጽና ሀገርን ለማሻገር ያለመ ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል። ፕሮጀክቱን በዋነኛነት የሚመሩት የብሬክስሩ ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ ስብሳቢ አቶ ነጻነት ዘነበ (Hypnotherapist) ናቸው።

የቦርድ ስብሳቢ አቶ ነጻነት ዘነበ እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተሰኘው መንግስታዊ ድርጅት ጋር በመተባበር የተሰናዳ መሆኑን ገልፀዋል። በቀጣይ 8 አመታትም በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የሚተገበር መሆኑን እና 20 ሚሊዮን ወጣቶችን ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን ገልጸዋል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማው በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣቶች ስልጠና በመስጠት ስብዕናቸው የታነጸ፣ ህይወታቸው የተለወጠ፣ ለሀገራቸውና ለወገናቸው ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶችን ማብቃት መሆኑን አመላክተዋል። በዚህም ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ከፍታዋ ለመመለስ በሚደረገው ጥረት በባለቤትነት ስሜት የሚረባረቡ ወጣቶችን ለማፍራት እንደሚሰራ መግለፃቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልፀዋል። 

በመጨረሻም ለትውልድ ወሳኝ የሆነው ይህ ሀገራዊ ፕሮጀክት ስኬታማ እንዲሆን የክልልና የከተማ አስተዳደር የስራ አስፈፃሚ አካላት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

"አልፋ ለስኬትዎ ጉልህ ድርሻ"