ትምህርታዊ ስልጠናዎችን በመሸጥ 206 ሚሊዮን ብር ማግኘት መቻሉን ብሬክስሩ አሳዉቋል።

ትምህርታዊ ስልጠናዎችን በመሸጥ 206 ሚሊዮን ብር ማግኘት መቻሉን ብሬክስሩ አሳዉቋል!

(ካፒታል : ጥር 15፤2016 ዓ.ም.)

በኢትዮጵያ በግል ስብእና ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን እየሰጠ ላለፉት 4 ዓመታት መቆየቱን የሚገልፀዉ ብሬክስሩ ትሬዲንግ አክስዮን ማህበር በተለያዩ ትምህርታዊ ፓኬጆችን በመሸጥ በተጠናቀቀዉ ዓመት 206 ሚሊዮን ብር ማግኘቱን ገልጿል።

የሼር እና ኔትወርክ ማርኬቲንግ ካምፓኒ ሆኖ በ17 ሰዎች የተመሰረተው ብሬክስሩ ከ 41 ሺህ በላይ አባላቶችን በመያዝ የስብዕና ግንባታን እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጿል።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አብድል ፈታ  "ሰዎች ዝንባሌያቸውን እና ህልማቸውን እንዲያዉቁ በሳይንሳዊ መልኩ ስልጠናዎች እንሰጣለን ይህንን ለመዉሰድ ክፍያ ይፈፅማሉ" በማለት ተናግረዋል።

ቅን እና ባለዕራይ ሰዎችን መፍጠር ዓላማው እንደሆነ የገለፀዉ ካምፒኒዉ በስልጠናው ሰዎች ህልማቸውን እንዲያዉቁ ከተደረገ በኃላ በተለያዩ መልኩ ስልጠናዎችን በመስጠት እራሳቸውን እንዲፈልጉና የግላቸውን ቢዝነስ እንዲጀምሩ እንዲሁም ከብሬክስሩ ጋር አብረዉ እንዲሰሩ አማራጭ እንሰጣለን በማለት አስረድተዋል ።

ስልጠናውን ከወሰዱ ከ41 ሺህ በላይ ሰዎች መካከል ከ 10 ሺህ በላይ የሚሆኑት የራሳቸውን የገቢ ምንጭ ፈጥረዉ በቋሚነት እየሰሩ እንደሚገኙ አብድል ፈታ ሁሴን ተናግረዋል።

ብሬክስሩ ትሬዲንግ አክስዮን ማህበር በዚህ ዓመት ለስልጠና ከሚያቀርባቸው ፓኬጆች በዚህ ዓመት 1 ቢሊዮን ብር ለማግኘት እቅድ እንዳለዉ አሳዉቆ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በኬንያ ፣ በደቡብ አፍሪካ ፣ በደቡብ ሱዳን ፣ እስራኤል እና ስዊድን ቅርንጫፎች መክፈቱን እንዲሁም ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል ።