"የኔ" የተሰኘ የሙያ ብቃት የሚጨምር የኦንላይን አጋር የሙያ መሳሪያ ምርት በድርጅታችን ብሬክስሩ ይፋ ተደረገ።

"የኔ" የተሰኘ የሙያ ብቃት የሚጨምር የኦንላይን አጋር የሙያ መሳሪያ ምርት በድርጅታችን ብሬክስሩ ይፋ ተደረገ።


“የኔ” ምርት በአለምአቀፍ ደረጃ እና በሀገር ውስጥ ባሉ ኩባንያዎች ውስጥ በከፍተኛ እና በስነ-ልቦና ጥናታዊ የተደገፈ ሲሆን፤ የቅጥር ብቃትን የሚጨምር መሳሪያ ነው። “የኔ” ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ ላሉ ተማሪዎች እና ለማንኛውም ሰው የሚሆን ሲሆን፤ በስነ-ልቦና የተረጋገጠ ምርት እንደዚሁም በሆላንድ ኮድ እና 250 የመረጃ ነጥቦችን በመጠቀም አንድ ሰው ምን አይነት ስብዕና እንዳለው ለመለየት እና የትኛውን የሙያ መስመር መከተል እንዳለበት ለማወቅ የሚረዳ ነው።


የድርጅታችን የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ነፃነት ዘነበ(ኢፕኖቴራፒስት) ባደረጉት ንግግር "በደቡብ አፍሪካ 150ሺ ወጣቶች ተጠቃሚ የሆኑበት ይህ ምርት አሁን በኢትዮጵያ ወጣቶች እስከ 4ሺ የክህሎት ስልጠናዎችን በመውሰድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል የመፍትሄ አካል ነው ይዘን የመጣነው" ብለዋል።


"የኔ" ሰዎች ማንነታቸውን አውቀው ከማንነታቸው ጋር የሚሄድ የትምህርት ዘርፍ እንዲመርጡ የሚረዳቸው ሲሆን በዚህም ምክንያት በተፈጥሮ ያላቸው ዝንባሌ እና ጥንካሬ ላይ ተመርከዘው የትምሀርትም ሆነ የስራ ዘርፋቸውን ስለሚመርጡ ደስተኛ እና ውጤታማ ሆነው እንዲማሩ ብሎም ህይወታቸው ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ውጤታማ እንዲሆኑ ታላቅ አስትዋፅዖ የሚያደርግ ምርት ነው። በተጨማሪም ተማሪዎች ስኮላርሺፖችን እንዲያገኙ የተለያዩ የኮሌጆችን እና ዩኒቨርሲዎችን መረጃዎች በየኔ ኦንላይን መድረክ ላይ በማግኘት አለምአቀፋዊ ዕድሎችን ተማሪዎች እንዲያገኙ ያግዛል።


"የኔ" ምርት ከየንዛ (Yenza) እና ከደቡብ አፍሪካ ስታንዳርድ ባንክ (Standard Bank) ጋር በመተባበር የበለፀገ አለምአቀፍ የኦንላይን የሙያ መሳሪያ ምርት ነው።